Dear Ethiopian Community Members
We would like to bring to your attention the state of the community center building at 4400 Chestnut Street. As you may have noticed, the front of the building on the 44th street side has a structural problem that needs immediate attention. We have also received a building violation notice from the License and inspection department of the city and are working closely with the inspector assigned.
Please find attached pictures that show the extent of the damage and its urgency.
We have been trying to address the issue without incurring a huge cost to the community for sometime and we currently have an engineer’s report in our hand. Three contractors have looked at the job and have already been given the engineer’s report and we are waiting for their estimate. For safety reasons, we no longer have a tenant to occupy the building. Therefore, the community does not have a source of income to cover monthly utility expenses.
As soon as the board decides as to which contractor to use and finalize the cost we will schedule a zoom meeting to update the membership.
Should you have any questions or suggestions please contact us at ethcomstaff@gmail.com and phone 215-222-8917
Housing Committee Members
Alem Kebede
Fikru Bekele
Ephrem Abraham
Amha Tadesse
ለኢትዮጵያ ማህበር አባላት በሙሉ
ይህችን ደብዳቤ ለውድ የማህበራችን አባላት መጻፍ ያስፈለገን ምክንያት፣ የኮሚኒቲ ማህበራችን ዋና ጽሕፈት ቤት ህንፃ በአሁኑ ወቅት ያለበትን ከባድና አሳሳቢ ሁኔታ ሁላችሁም በጥብቅ እንድትገነዘቡት ለማድረግ ነው።
የዚህ ደብዳቤ እባሪ አድርገን የላክናቸሁን ፎቶግራቾች በመቃኘት እንደምትረዱት፣ በ44 ቸስትነት ስትሪት (44th and Chestnut Street) በኩል ያለው የማህበራችን ህንፃ ግድግዳ የመዋቅር ችግር ስላጋጠመውና አስቸኳይ ጥገና ስለሚያስፈልገው፣ የማህበራችን አባላት በሙሉ ለዚህ ችግር ትኩረት መስጠት እንዳለባችሁ ለማሳሰብ እንወዳለን።
ከዚህ የህንፃችን ችግርም ጋር በተያያዘ፣ ከፊላደልፊያ ከተማ የፈቃድና የመርማሪ ክፍል፣ ስለህንጻው ጉድለት ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠንና ከተመደበልን ኢንስፔክተርም ጋር ጉዳዩን በሚመለከት እየሰራን መሆናችንን እንድታውቁልን ይሁን። ከላይ እንደገልጽነው፣ የህንጻው ጉዳትና የጥገናው አስቸኳይነት በበለጠ ለመረዳር ከዚህ ጋር የተያያዙትን ፎቶግራፎችም ይመልከቱ።
በኡሁኑ ወቅት የኢንጂነር ሪርፖርት በእጃችን የሚገኝ ሲሆን፣ በተጨማሪም ሶስት (3) ኮንትራክተሮች የኢንጂነሩ ሪፖርት ተሰጥቷቸውና ህንፃው የሚያስፈልገውን ስራ እራሳቸው ተመልክተው፣ የሚሰሩበትን የዋጋ ግምት እስከሚሰጡን ድረስ እየጠበቅን ነው። በተቻለ መጠንም ችግሩን በአነስተኛ ወጪ ለማሰራት ትልቅ ጥረት በማድረግ ላይ እንደምንገኝ እንድታውቁልን እንወዳለን። የቦርድ አባላት የሚቀጥሩትን ኮንትራክተር የትኛው እንደሆን ሲወስኑና የሚሰራበትን የዋጋ ተመን ሲያውቁ፣ ስላለው ሁኔታ አጠቃላይ መግለጫ ለአባላት በሙሉ ለመስጠት ጠቅላላ ስብሰባ በዙም (zoom) እንደምንጠራም በቅድሚያ እናሳውቃለን።
አስፈላጊውን ጥንቃቄ መውሰድ ስለሚያስፈልግ፣ የሚከራየውን የማህበሩን የህንፃ ክፍል ተከራይተው የነበሩት ግለሰቦች ለጊዜው ለቀው እንዲወጡ በመደረጉ፣ በአሁኑ ወቅት ኮሚኒቲው የወር ወጪውን የሚሸፍንበት ገቢ እንዳጣ ብትረዱልንም መልካም ነው።
ይህንን በተመለከተ፣ ያላችሁን ጥያቄ/ዎች ወይም አስተያየት/ቶች በዚህ ኢሜል አድራሻ (ethcomstaff@gmail.com) ቢልኩልን ወይም በዚህ ስልክ ቁጥር (215-222-8917) ቢደውሉልን ይደርሰናል።
ከማክበር ሰላምታ ጋር፣
ከቤቱ ኮሚቲ አባላት
አለም ከበደ
ፍቅሩ በቀለ
ኤፍሬም አብርሃም
አምሃ ታደሰ